Blog Details

img
IT & Software

ማንኛውም ሰው ኮምፒውተራችሁ ላይ flash እንዳይሰካ እንዴት የኮምፒውተራችሁን USB port temporarily disable ማድረግ ትችላላችሁ።

Big / 26 Dec, 2023

ማንኛውም ሰው ኮምፒውተራችሁ ላይ flash እንዳይሰካ እንዴት የኮምፒውተራችሁን USB port temporarily disable ማድረግ እደምትችሉ ላሳያችሁ።

በሁለት አይነት ዋና ዋና መንገዶች disable ማድረግ ትችላላችሁ።
1ኛ በwindows setting
           ✅Device manager
           ✅Group policy editor
✅በDevice manager ለመቆለፍ
Windows start button ነክታችሁ device manager ብላችሁ ጻፉ።
ከሚከፈትላችሁ ውስጥ ታች ላይ Universal Serial Bus controllers የሚል ምርጫ አለ። ስትከፍቱት የUSB ፖርቶቹ ይዘረዘሩላችኋል። እየመረጣችሁ right click አድርጉና disable አድርጉት።
enable ማድረግ ከፈለጋችሁ ደግሞ በተመሳሳይ step ሄዳችሁ enable ታደርጋላችሁ።
✅በGroup policy Editor ለመቆለፍ
🧡Windows key + R ነክታችሁ Run dialog box ይከፈትላችኋል።
🧡"gpedit.msc" ብላችሁ ፃፉና ok ብላችሁ ክፈቱት።
🧡#Computer_configuration ከሚል ፎልደር ውስጥ #Administrative_Templates ከዛ #System ከዛ #Removable_Storage_Access የሚለውን ስትከፍቱ...
🧡Removable Disks: Deny Execute Access
🧡Removable Disks: Deny Read Access
🧡Removable Disks: Deny Write Access
የሚሉ አሉ ሶስቱንም እየከፈታችሁ #Enable አድርጉና #Apply #OK ስትሉት ሁሉም USB ፖርቶች disable ይሆናሉ።
🧡Enable ለማድረግ ተመሳሳይ step ሄዳችሁ Disable ስትሉት ፖርቶቹ enable ይሆናሉ።
ከላይ የዘረዘርኩላችሁን መንገዶች ለመጠቀም administrator account ላይ መሆን ይኖርባችኋል።

2ኛው መንገድ 3rd party ሶፍትዌር መጠቀም
USB port blocker ብዙ ሶፍትዌሮች ቢኖሩም በጣም ቀላሉ ከታች ያስቀመጥሁላችሁ ነው።
ይህን ዳውንሎድ ካደረጋችሁ በኋላ install ማድረግ አይጠበቅባችሁም። ዝም ብላችሁ በመክፈት blockና unblock ማድረግ ትችላላችሁ።

0 comments