Microsoft በተለያየ ጊዜ የሚያወጣቸውን Windows OS በርካታ edition አላቸው። እያንዳንዱ edition የተጠቃሚዎችን አይነትና ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው። ዋናዎቹ ኢዲሽኖች Windows 10 Pro፣ Windows 10 Home እና Windows 10 Enterprise ናቸው። እያንዳንዱ edition የራሱ የሆኑ features አሏቸው። አጠቃላይ ትርጉምና ልዩነቶቻቸው እነሆ፡-
Windows 10 Home:
Windows 10 Home የWindows 10 መሠረታዊ edition ሲሆን ኮምፒውተርን ቤት ውስጥና ለመሰረታዊ ተግባሮች ለሚጠቀሙ የተሰራ ነው። ኢንተርኔት ለመጠቀም ለሚዲያ ለጌሚንግና የተለያዩ ሶፍትዌሮችን ጭኖ ለመጠቀም ያገለግለናል።
የWindows 10 home መሰረታዊ ፊቸሮች
✅Microsoft digital assistant (cortana)
✅Microsoft edge browser
✅Windows Defender antivirus
✅Windows Ink for digital pen support ናቸው።
Windows 10 Pro:
Windows 10 Pro አድቫንስድ የሆነ የዊንዶስ ኢዲሽን ሲሆን ትናንሽና መካከለኛ ቢዝነስ ያላቸው ተጠቃሚዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ነው። የhome ሁሉንም ፊቸሮች ጨምሮ ተጨማሪ ቢዝነስ ነክ የሆኑ ፊቸሮችን ከsecurity, ከማኔጅመንትና ከproductivity አንጻር ያካተተ ነው።
ከነዚህም መካከል
✅BitLocker encryption
✅Remote Desktop
✅Group Policy Management ናቸው።
Windows 10 Enterprise:
Windows 10 Enterprise ዲዛይን የተደረገው ለትልልቅ ድርጅቶችና ኢንተርፕራይዞች ነው። ሁሉንም የWindows 10 pro ፊቸሮች አጠቃሎ ተጨማሪ ውስብስብ የIT ስራዎችን ለማቀላጠፍ የሚረዱ እንደ
✅Windows To Go
✅DirectAccess
✅AppLocker
✅Credential Guard የመሳሰሉ ፊቸሮችን ይይዛል።
በአጠቃላይ ኮምፒውተራችሁ ላይ Windows 10 ስትጭኑ ኮምፒውተራችሁን እንደምትጠቀሙበት የስራ አይነት ኢዲሽኑንም መወሰን አለባችሁ። ለምሳሌ ብዙ ሰው BitLocker encryption መጠቀም ይፈልግና ኮምፒውተሩ ላይ የተጫነው ግን Windows 10 home ይሆናል። ከዛ ሲያጣው ግራ ይጋባል። ስለዚህ እንዚህን ነገሮች ታሳቢ ማድረግ አለባችሁ።
0 comments