Hacking ምንድን ነው?
Big
/ 26 Dec, 2023
Hacking ከመማራችን በፊት ምን እንደሆነ ማወቅ ስለሚኖርብን ይህን Episode በHacking እና በHacker ዙሪያ እናወራለን።
🔺Hacking ምንድን ነው?
Hacking ማለት ኮምፒተርን በመጠቀም የኮምፒተርን ስርዓትን ወይም የግል ኔትወርክን ሰብሮ በመግባት መረጃ ለመበዝበዝ የሚደረግ ሙከራ ነው።
ነገር ግን Hacking ስንል ሁልጊዜ ለመጥፎ ተግባር የሚውል አይደለም አንዳንድ ተቋማት የኮምፒውተር እውቀት ያላቸውን ሰዎች በመቅጠር የራሳቸውን ሲስተም ሰብረው እንዲገቡ ያበረታታሉ።
ከዚያም እነዚህ ቅጥረኛ ሀከሮች ሰብረው ሲገቡ የገቡበትን ደካማ ጎን በማሻሻል ሲስተማቸውን ያጠናክራሉ።
🔺Social Engineering ምንድነው?
በቀላል አማርኛ የሰዎችን ጭንቅላት Hack ማይረግ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ስለHacking ስናስብ ሙሉ ስራው ኮምፒውተር ለይ የሚያልቅ ይመስለናል ነገርግን አንድ ሀከር ለምሳሌ ማልዌር የሚጠቀም ከሆነ ያንን ማልዌር የሚፈልገው ሲስተም ለይ እንዲሰራጭ ሰዎችን በማታለል የማውቁትን Email እንዲከፍቱ አሳማኝ ውሸት ማዘጋጀት ይኖርበታል።
በመሆኑም ይህ ሰዎችን እምነት በማግኘት ሰዎችን የማታለል ጥበብ ለሀከሮች በጣም ጠቃሚ ነው።
🔺ስንት አይነት ሀከሮች አሉ?
◽️ White Hat Hacker:
በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ሀከሮች በሀኪን ዙሪያ ቀላል የማይባል እውቀት ያላቸው ሲሆን እውቀታቸውን በህጋዊ መንገድ የሚጠቀሙ ናቸው። እነዚህ ሀከሮች የኢንተርኔት የሲስተሙን የደህንነት ጥንካሬ ለማረጋገጥ Penetration Testing የሚሰሩ ናቸው።
◽️ Black Hat Hackers:
የኮምፒውተር እውቀታቸውን ህገወጥ ለሆነ መጥፎ ተግባር የሚጠቀሙ ናቸው። ማለትም የአንድን ሲስተም ደካማ ጎን አጥንተው የተለያዩ መረጃዎችን በመስረቅ የሚሸጡ ወይም የሚያጠፉ ናቸው። በቀላል አነጋገር ከመስረቅ ጀምሮ ፣ የሕዝብ መረጃ መጥለፍ ፣ መለወጥ ብሎም በኢንተርኔት ማዕቀፎች ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በመጠቀም ዝናን ወይም የገንዘብ ጥቅሞችን ለማግኘት ይሰራሉ።
◽️ Grey / Brown hat hackers:
እነዚህ ሀከሮች ብዙውን ጊዜ ድብልቅ ዓላማዎች አሏቸው። ልክ እንደ ቀለሙ ይህ የሀከር ዓይነት የነጭ ኮፍያ ጠላፊ መልካም ዓላማ የለውም ፣ የጥቁር ጠላፊም መጥፎ ፍላጎት የለውም ፡፡ ይህ ሀከር ሲስተሞችን ሰብሮ ይገባል ነገር ግን ለራሱ ጥቅም አይደለም። ዝነኛ Grey Hat ሀከሮች የመንግስታትን ሚስጥር ለህዝቡ በማጋለጥ ይታወቃሉ።
Hacking ለመጀመር የሚያስፈልጉንን ነገሮች
◽️ በመጀመሪያ ደረጃ Professional ሀከር ለመሆን ከፈለግን Major የሚባሉ የProgramming language Master ማድረግ ይኖርብናል።
🔺ለመጀመሪያ ደረጃ ግን እነዚህን ብንችል ይመረጣል።
◽️ C Programming
◽️ C++ Programming
◽️ Python ሌሎችም........
ከእነዚህ ቡሀላ የምንሰራበትን Environment ማስተካከል ይኖርብናል። የምንጠቀምበትን Operating System መምረጥ አለብን Windows የሚባል Operating System ተጠቅመን ሀኪንግ መጀመር አንችልም።
ስለዚህ የተለያዩ የLinux Operating System መጠቀም ይኖርብናል። ከእነዚህም መሀል በጣም ታዋቂ የሆነውን የKali Linux መጠቀም እንችላለን። Kali Linux ለHacking እና Penetration Testing ተብለው የተሰሩ ቱሎችን በውስጡ ይይዛል።
🔺ለምሳሌ ለመጥቀስ
◽️ Hydra
◽️ Wifite
◽️ NMap
◽️ ZenMap
◽️ WireShark
◽️ MetaSploit
◽️ Aircrack-ng
◽️ John the Ripper
◽️ Kali Linux Almost ሙሉ ስራውን ይጨርሳል። ይህን Operating System ከWindows ጋር ጎን ለጎን መጠቀም ለምትፈልጉ ከታች ባለው Link አውርዳቹ መጠቀም ትችላላቹ።
🔺Kali Linux Pc 64bit ISO:
https://www.kali.org/get-kali/#kali-platforms◽️ በስልካችሁ ለምትሰሩ ቤተሰቦቻችን ደግሞ Kali Linux Android ለመጫን የሚከተሉትን አፖች አውርዳቹ መጠቀም ትችላላችሁ።
◽️ Linux Deploy
◽️ Android VNC Viewer
0 comments